Wednesday, March 7, 2018

የካቲት 16 የራስ ደስታ ዳምጠው እና የደጃዝማች በየነ መርዕድ 81ኛ የጀግና የሙት ዓመት መታሰቢያ


የካቲት 16 የራስ ደስታ ዳምጠው እና የደጃዝማች በየነ መርዕድ 81 የጀግና የሙት ዓመት መታሰቢያ



1929 / - በግራዚያኒ የሚመራ የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት በዝዋይ አካባቢ የጦር አዝማቾቹን የራስ ደስታ ዳምጠውን እና የደጃዝማች በየነ መርዕድን አርበኞት ድል አደረጉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን አዝማቾች ሕይወታቸውን በዚህ ዕለት ሰዉ። ኢጣሊያውያኑ ራስ ደስታን ከያዟቸው በኋላ በጥይት ደበደቧቸው፡፡
ደጃዝማች በየነ መርድ የባሌ አገረ ገዥና የልዕልት ሮማነወርቅ ባለቤት ነበሩ። ጣልያ ኢትዮጵያን በወረረው ጊዜ 1928 .. ጀምሮ ታዋቂ አርበኛ ሲሆኑ 1929.. ተይዘው ተገደሉ። የደጃዝማች መርድ በየነና የደጃዝማች ሶምሶን በየነ አባት ነበሩ።


ራስ ደስታ ዳምጠው

ራስ ደስታ ዳምጠው ሰሜን ሸዋ ውስጥ ተወለዱ። አባታቸው ፊታውራሪ ዳምጠው ከተማ በአደዋ ዘመቻ ትልቅ ጀብደኝነት እንደተሰው ይነገራል። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዎ እንደነበራቸው የሚነገርላቸው ራስ ደስታ ለዚህ አስተዋፅዋቸው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ልጃቸውን ተናኝወርቅ ኃይለሥላሴ ድረውላቸዋል።

ራስ ደስታ የውጭ አለማትን የመጎብኝት እድል ስላጋጠማቸው የውጭውን ስልጣኔ ወደሃገራቸው ለማምጣት እንደ ሰፊ መንገድ፣ የንፁህ ውሃ አገልግሎት፣ ህክምና፣ትምህርት ለማስፋፋት የበኩላቸውን ቅስቀሳ ያደርጉ ነበር። ጣሊያን ወረራ ባደረገ ጊዜ ራስ ደስታ የሲዳሞ አገረ ገዥ ነበሩ። በመሆኑም በነገሌ ቦረና በኩል የመጣውን ጠላት ለመመከት ወደዚያው ዘመቱ። በሱማሊያም በኩል የመጣውን ጠላት ማጥቃታቸው ይገለፃል። ትልልቅ ውጊያዎችንም በማይጨው ላይ ከደጃዝማች በየነ መርዕድ ጋር አካሂደዋል። ራስ ደስታም ለአንድ ዓመት ያህል ከተዋጉ በሗላ በጠላት ጦር የካቲት 16 ቀን 1929 . . ተገድለዋል። ለመዘከርም አዲስ አበባ ውስጥ በስማቸው የሚጠራ ሆስፒታል ተሰርቶላቸዋል።


ራስ ደስታና ደጃዝማች በየነ መርድ (ሸዋ ያፈራቸው የኢትዩጵያ ጀግኖች) ከጠላት ጋራ ያደረጉት ጦርነት

የኢጣልያ ጦር በታንክና በቦምብ እየተረዳ ሰሰበኒን፣ ገርሎግቢን፣ ቆራሔን ከያዘ በኃላ ጦርነቱን ወደ ፊት ለመቀጠል ይዘጋጅ ነበር። ከመቁዋዲሾ ወደ አዲስ አበባ የሚያስመጣው በሁለት አቅጣጫ ነው።

አንደኛው: - ከመቁዋዲሾ - በለደወይን - ቆራሔ - ደጋህቡር - ጅጅጋ -ሐረር - አዲስ አበባ።
ሁለተኛው: - ከመቁዋዲሾ - በይደዋ - ሉክ - ዶሎ - ነገሌ - ይርጋዓለም - ሞጆ - አዲስ አበባ ነው።

የግራዚያኒ ጦር ዋና ሐሳቡ በቆራሄና በደጋህቡር በኩል አልፎ ሐረርጌን ለመያዝ ነው። ነገር ግን ይህ ጦር ወደ ጅጅጋ በሚያመራበት ጊዜ: የራስ ደስታ ጦር በዥርባው በኩል አልፎ ሱማሊያን እንዳይወርበት: በቆራሄ ግንባር ተከላካይ ወታደር ብቻ አስቀምጦ: ዋናውን ጦር ወደ ዶሎ ሄዶ እንዲከላከል አደረገ።

ክቡር ራስ ደስታም ዋና ዋና አሽከሮቻቸውን
-ፊታውራሪ አደመንና 
-
ፊታውራሪ ታደመን
እፊት አስቀድመው: እርሳቸው በኃላ ደጀን ሆነው: ወደ ፊት እየገፉ እስከ ኢጣልያ ግዛት እስከ ዶሎ ጫፍ ደርሰው ነበር። በዚህም ግዜ ከኢጣልያ ሱማልያ ግዛት ውስጥ ታላቅ ፍርሃት ተነዝቶ ነበር።
በዚህም ምክንያት: ግራዚያኒ በሱማልያ ያለው መቶ ሺህ ጦር የሚበቃኝ አይደለምና: ሌላ ረዳት ላኩልኝ እያለ ወደ ሙሶሎኒና ወደ ባዶልዩ ቴሌግራም ያስተላልፍ ነበር።
ባንድ ወገን ደግሞ: በሱማልያ ግዛት ውስጥ በመቁዋዲሾ፣ በሜርካ፣ በጀናሌ፣ በአውደግሌ፣ በቡሎቡርቲ፣ በበለደ ወይንና በሌላውም በየመንደሩ ነዋሪ ሱማሌዎችን ባዋጅ እየሰበሰበ
"ይሄው ኢትዩጵያውያን ሱማሊያን ለመውረር ተሰልፈዋል። 
እኛም እንደሚገባ ተዋግተን ድል የሆንን እንደ ሆነ: በመርከባችን ተሳፍረን ወዳሀገራችን እናመልጣለን። 

እናንተ ግን የምትሄዱበት ስፍራ የላችሁምና በወረሩዋችሁ ግዜ: -
---ወንዶቹን እየሰለቡ 
---
ሴቶቹን ጡታቸውን እየቆረጡ ይበሉታል።
ምግባቸውም የሰው ስጋ ነው።
ስለዚህ እኛ ድል ሳንሆን: ነጋዴ ነን፣ ገበሬ ነን ሳትሉ ባንድነት እንዋጋ።" እያለ ሐሰት የመላበትን ወሬ እየዞረ ይሰብክና ያሰብክ ነበር።
የሱማሌ ሕዝብም እውነት እየመሰለው: ገበሬውም፣ ነጋዴውም ወደ ኢጣልያ መጋዘን እየቀረበ ስሙን እያፃፈ፣ ብረት እየተቀበለ ከሊቢያ ወታደሮች ጋር ሆኖ ለውጊያ ተሰለፈ።


ምንጭ:
 - ተክለ ፃድቅ መኩሪያ ከአፄ ቴዎድሮስ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ገፅ 269-271
-
ታሪካዊ እዝገበ ሰብ፣ ውክፔዲያ

 ክብር ለተሰውት ጀግኖቻችን