Wednesday, March 7, 2018

የካቲት 26


1945 . የካቲት 26 በዛሬው ዕለት ጆሴፍ ስታሊን በሞት ተለዩ፡፡ 65ተኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ

Mulugeta Anberber


የሶቪዬት ሕብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን 1870 .. ተወለደ እና 1945 .. ሞተ። ከምሽቱ ለሦስት ሰዓት አሥር ጉዳይ ላይ እንደሞቱ ተገለጸ።

የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት መሪ፣ ጆሴፍ ስታሊን፣ 20ኛው ክፍለ ዘመን፣ ታላላቅ መሪዎች አንዱ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ ሰውየው፣ በሶቪየት ህብረት ታሪክ፣ በክፉና በበጐ ይነሳል፡፡ ግን ክፉው ሚዛኑ ይደፋል ይባልለታል፡፡ ጆሴፍ ቫላሳሪዮቬች ስታሊን፣ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው፣ የዛሬ 65 ዓመት፣ በዛሬዋ እለት ነው፡፡ ከሩሲያው፣ 1917 የጥቅምት አብዮት በኋላ፣ የአብዮቱ መሪ፣ ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን፣ በፀና ሕመም አልጋ ላይ መዋሉ፣ ስታሊን መሪነቱን እንዲይዝ፣ መንገድ ከፈተለት፡፡ ሌኒን፣ በሕይወት ዘመኑ መጨረሻ፣ የስታሊን ክፋት፣ መሠሪነትና ጭቦኝነት፣ ስላስጋው አድራጊ ፈጣሪ ከነበረው፣ የቦልሼቪኮች የፖለቲካ ማህበር እንዲባረር ፍላጐቱ ነበር፡፡ አጅሬ ስታሊን ግን፣‹‹ የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል›› አይነት ሆነ፡፡ በመሠሪ ባሕሪው የዘመኑን ቱባ ቱባ ሹሞች፣ አንዱን ከሌላው እያላተመ፣ ስልጣኑን አደላደለ፡፡

ለውጭም ሆነ ለውስጥ ተቃዋሚዎቹ፣ እንጥፍጣፊ ትዕግስት አልነበረውም፡፡ 
ተቃዋሚዎቹንና ተችዎቹን፣ ድምጥማጣቸውን ለማጥፋት ተኝቶ አያድርም፡፡ 
ለምሳሌም፣ በላቀ ምሁርነቱ፣ ይታወቅ የነበረውን ሊዮን ትሮትስኪን፣ ከስልጣን አባረረ፡፡
የአገር ውስጥ የቁም እስረኛ አደረገው፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ግዞት ላከው፡፡

ግዞት በሄደበትም፣ በራቀው የዓለም ክፍል፣ በሜክሲኮ እንዳለ፣ ባለመጥረቢያ ነፋሰ ገዳይ ላከበት፡፡ ሕይወቱንም ቀጠፋት፡፡

ለቁጥር የሚያታክቱ ዜጐች፣ የገዛ የፖለቲካ ማህበሩ አባሎች ሳይቀሩ፣ የአብዮት የሕዝብ ጠላቶች፣ እየተባሉ፣ እንዲፈጁ አድርጓል፡፡- በስታሊን የተፈጁት፣ ቤቱ ይቁጠራቸው የሚባልላቸው ናቸው፡፡

ዘግናኝ የሆነው፣ የቀይ ሽብር ፍጅት ሲታወስ፣ በዛም ሆነ በዚህ፣ የፍጅቱ መሐንዲስ የሆነው የስታሊን ስም ይነሳል፡፡ 

ሰውየው በብዙዎች ደም የዋኘ ነበር፡፡

ስታሊን፣ በፈፀመው የበረከተ ፍጅት፣ ስሙ ጥላሸት ቢቀባም፣ የሶቪየት ቀይ ጦር፣ 2ኛው የዓለም ጦርነት፣ በናዚ ጀርመንና በተባባሪዎቿ ላይ ለተቀዳጀው ድል፣ ታላቅ ድርሻ በማበርከት ይታወቃል፡፡

አገሪቱ፣ የታላላቅ ኢንዲስትሪዎች ባለቤት እንድትሆን ማስቻሉ፣ ይመሰከርለታል፡፡
ለሶቪየት ሕብረት፣ የኒኩሊየርና የሌሎች ታላላቅ የጦር መሳሪያዎች ባለቤትነትዋ፣ የስታሊን መሪነት ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡

የአገሪቱ የስለላ ተቋምም፣ ረቀቅና መጠቅ ወዳለው አቋሙ የተሸጋገረው፣ በስታሊን የአመራር ዘመን ነው፡፡

በሽኩቻ ውስጥ አልፎ፣ ወደ ስልጣን የመጣው ስታሊን፣ 20 ዓመታት በላይ ከዘለቀው አገዛዙ በኋላ፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡ በተራው፣ የሱም ስልጣን ሌሎቹን ሹሞች ያሻኩት ጀመር፡፡

በሽኩቻው ኒኪታን ኩርቺየቭ፣ አሸናፊ ሆነው የስታሊን ስልጣን ጨበጡ፡፡ 
ኒኪታን ኩርቺየቭ ስልጣን ላይ ከወጡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የስታሊንን አምባገነናዊ ሐጢያት ዘከዘኩት፡፡

የስታሊን የቀብር ስፍራ ከክሬምሊን ተነሳ፡፡ ሐውልቶቹ ከብዙ የሶቪየት ግዛቶችና ከተሞች ተፈነቃቀሉ፡፡ -‹‹ጓድ ስታሊን ለዘላለም ይኑሩ!›› የተባለለት ሰው ከሞቱ በኋላ የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛዋል አይነት ሆነበት፡፡

1914 .. እስከ 1945 .. ድረስ የሶቭየት ኅብረት መሪ ነበር። 

የሶቪዬት ሕብረት መሪ ጆሴፍ ስታሊን ከምሽቱ ለሦስት ሰዓት አሥር ጉዳይ ላይ እንደሞቱ ተገለጸ። ምትካቸው ኒኪታ ክሩስቾቭ ነበሩ።

ነፍስ ይማር


ምንጭ 
ሸገር ድኀረ ገጽ
እና
ልዩ ልዩ


No comments:

Post a Comment