Friday, January 26, 2018

ይሰማል ሸዋ!

ይሰማል ሸዋ!


ይሰማል የእምዬ ልጆች!
ዜዶ ነኝ ጎጃሜው….
እያጉረመረመ እያጉረመረመ
ያ ጎጃሜ ልቤ ሸዋ ላይ ከረመ
በሸዋ ልጅ ፍቅር በደብረ ሲናዋ
ወደቀና ልቤ ከዘረ ጀግናዋ
የምኒሊክ ወኔን ካባቷ ዋጅቼ
የበላይን ቁጣ ከራሴ ቀድቼ
በፍቅር ላሰክራት ይችን የሸዋ ልጅ
እንከራተታለሁ ተይዤ እጅ ከፈንጅ
‹‹አንተ የበላይ ዘር ጅንኑ ጎጃሜ
ደረቴ ላይ እደር ጠቶቼ ላይ ተኛ ልበልህ ደግሜ ››
እያለች በዜማ ወኔና ስሜቴን እንድታሞካሸው
ዝናሬን አጥብቄ ሲና ላይ ልክረመው፡፡
(አቦ ሸዋ በጀግንነትም በፍቅርም ነው እንዴ የሚያሸንፈው !)
(ዘላለም በላይነህ)

No comments:

Post a Comment