Sunday, January 28, 2018

የተሀድሶ ብዛት



የተሀድሶ ብዛት
.
 በሙሉጌታ አንበርብር  
.
ነገሩን አትፍራ 
ድፈር አትጠምዘዝ 
በሃሰት መንገድ ላይ እውነትን ተመርኮዝ
ውሸት ገፈታትሮ ገደል ላይ ቢያቆምህ 
እንደው አቅም ኑሮት ካሮንቃ ቢጥልህ
እውነት እልሃለሁ . . . 
እውነትን ተጋራ . . .
እያለ ይሰብካል እውነትን ሊዘራ
.
እውነትን ግን ምንድን ነው?
ሀሰትስ የማን ነው?
ብሎ ይጠይቃል መልስ ያጣ እሮሮ
ሀሳብና መልሱን የተቀማ አዕምሮ 
ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስለዋል
ያላዬውን ሁሉ በመስማቱ ያምናል 
በብኩን ሀገር ላይ ሞልቶል ተሀድሶ
.
ፀረ-ተሀድሶ . . .
ጥልቅ ተሀድሶ . . .
.
እያሉ እያምታቱ ኪሳቸው ይደልባል
ሆዳቸው ተገፍቶ ቀጠሮ ይያዛል
በነሱ ሆድ መግፋት እድገት ይታየናል
ሀሰት ስትኮሰምን እውነት ስፈነጥቅ
ትንሽ ወኔ አግኝቶ ጥያቄ ሲጠይቅ 
ህዝብ ትክክል ነው እያሉ እያሞኙ
ወተት በሌለበት ቅቤ ያነጥራሉ
ገዡ ገዝጋዥ ሁኖል . . .
ማለትም ይቻላል . . .
ተገዥ ተገዝግዞ መሀል መንገድ ቁሟል 
አውላላ ላይ ቁሞ እድሜውን ይፈጃል
የዕድገት ጀንበሩን ሁሌም ይገብራል
.
ጀንበር ከጠለቀች ጨረቃ ከሌለች 
ምን ጣይ መንግስት ቢኖር ጥልመቱ ይገዝፋል
መብራት አለ ብሎ ፋኖሱን ላጠፋ
ሰርኩ ያልነጋለት የዘመን ገዳፋ
ጨረቃ ለምኑ ጨረቃን ይመኛል
ጭራቅ ውጤት ሁኖ ጨረቃ ነኝ ይላል


No comments:

Post a Comment