Friday, January 26, 2018

ኢትዮጵያ . . . ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ሌላ ዋና ከተማ ለመቆርቆር እየታሰበላት ነው::

ኢትዮጵያ . . . ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ሌላ ዋና ከተማ ለመቆርቆር እየታሰበላት ነው
~~~~~~//~~~~~~~//~~~~~~//~~~~~~~~//~~~~~~~//~~~~~~~~



አዲስ አበባ ከተማ ከሀገሪቱ መዲናነት ባሻገር የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት መቀመጫ በመሆኗ የነዋሪዎቿ ቁጥር በየጊዜው በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ይገኛል፡፡ በዚህም ከትራንስፖርት አቅርቦት እስከ የመኖሪያ ቤትና ሌሎች ፍላጎቶች ድረስ ያለው እጥረት በየጊዜው እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል፡፡ በአዲስ አበባ የሚታየውን ሁለንተናዊ መጨናነቅ ለመቀነስም በአንዳንድ አገሮች ልምድ እንደሚታየው ከዋናው ከተማ ተቀራራቢ ሚና የሚኖረው ሁለተኛ ከተማን የማሰቢያ ጊዜ አሁን መሆኑ ይነሳል፡፡ 
በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የከተማ ልማት ጥናት ፋካሊቲ ምክትል ዲን አቶ እንግዳ ታዴ፤ አገሪቱ በዋና ከተማዋ ካለው ሁለንተናዊ ጫና አንፃር ሁለተኛ ከተማን ለማሰብ መዘግየቷን ይገልጻሉ፡፡ ይሁንና በቅድሚያ በከተሞች የሚታየውን ዕቅድን መሰረት ያላደረገ ዕድገትና መስፋፋት መስመር ማስያዝ ይገባል፡፡ የከተሞች መስፋፋት ሂደት በአብዛኛው ጤናማነት የጎደለው በመሆኑም ሊታሰብበት እንደሚገባ ያመለክታሉ፡፡
ከዓመታት በፊት የአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች በግብርና እምብዛም ምርታማ ባለመሆናቸው ምክንያት በአካባቢው ከማምረትና አካባቢውን ከማልማት ይልቅ በርካታ ሰዎች መሰደድን ምርጫ ያደርጋሉ፡፡ ይህም ከተሞች በዕቅድ ተመስርተው በዘመናዊ መንገድ የለሙ እንዳይሆኑ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ‹‹ይሄን መቀየር ይቻላል›› የሚሉት አቶ እንግዳ፤ ከተሞቹን መልሶ በዕቅድ (ፕላን) ለማልማት በከተማ አስተዳደሮች የቁርጠኝነት ችግር ይታያል፡፡ ይሄም አንዱን አካባቢ ከአንዱ ተመጣጣኝ እንዳይሆን አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ለከተሞች ልማት መዋል የሚገባውን ሃብትና በጀት በአግባቡ ባለመጠቀም፣ በቂ የስራ ዕድል ባለመፍጠር፣ ከትምህርት ተቋማት ጋር ተገቢውን ግንኙነት ባለማመቻቸታቸው ምክንያት የከተሞች ዕቅድ ኋላቀር እንዲሆን አድርጓል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ አርክቴክቸር ቢዩልዲንግ ኮንስትራክሽንና ከተማ ልማት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶክተር ጥበቡ አሰፋ፤ አዲስ አበባ ከተማ አሁን ከሚታዩባት ዘርፈ ብዙ መጨናነቆች አንፃር ሁለተኛ ከተማን ማሰብ አዋጭ ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ፤ አዋጭ መሆኑ እርግጥ ነው፤ ነገር ግን አቅሙ አለ ወይ? በማለት ጥያቄን በጥያቄ ያነሳሉ፤ አዲስ ከተማ ለመገንባት አቅም ከማስፈለጉም በላይ ምን ለማምጣት ነው የሚገነባው? የሚለውን በአግባቡ መመለስ እንደሚገባ ያሰምሩበታል፡፡
‹‹ከተማ ማለት ህንፃ መገንባት አይደለም›› የሚሉት ዶክተር ጥበቡ፤ በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ከተማ ምን ያህል በአግባቡ ተጠቅመንበታል? የሚለውን ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ እንደ እርሳቸው እምነት ሁለተኛ ከተማን ከማሰብ በፊት መቅደም የሚገባቸው በርካታ ነጥቦች አሉ፡፡ በቅድሚያ አሁን ያሉትን ሁሉንም ከተሞች ደረጃ ማሳደግና በአግባቡ መጠቀም ነው፡፡ ምክንያቱም ይላሉ፤ ከተማን መገንባት የሚያስፈልገውን ያህል ለተገነባው ከተማ አጠቃላይ ፍላጎት ማሟላት ካልተቻለ ከተሞች ከጥቅማቸው ይልቅ የወንጀል መስፋፊያ የመሆን ዕድላቸው ይሰፋል፡
ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ ተከታዩን ሊንክ/ማያያዣ ይጠቀሙ
http://ashammedia.simplesite.com/…/ኢትዮጵያ-ከአዲስ-አበባ-ተጨማሪ-ሌላ-ዋ…
#Eth_Press #Asham_Media #አሻም_ሚዲያ

1 comment: