Friday, January 26, 2018

የሚዲያው እጣ ፈንታ በመንግስት እጅ ሳይሆን በጋዜጠኛው አዕምሮ ውስጥ ነው ፡፡




/ተጻፈ በጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር/

* * የጉዞ ማስታወሻ * * 

ሁሉንም ነገር ሳዬው ሾላ በድፍን ይመስለኛል፡፡
  ከህፃንነት እድሜያችን ጀምሮ መሞከር የምንችለው እና መስራት የምነችለውን ነገር ኡፉነው፤ ለእሱ እድሜህ ባህሉ አይፈቅድም በሚል አጉል ጠቃሚ ባልሆኑ ምክሮች ታጥረን አደገን፡፡ እንኳን የማህበረሰቡን ችግሮች የራሱን ችግር ለማጋለጥ በራስ መተማመናችን ተሰልቧል፡፡ እያለ ሲናደድ የበታተነውን ፀጉሩን ጨምሮ ቦጫጨረው፡፡
ካሉት የልማታዊ ጋዜጠኞች መካከል ስምዖን ከአፍንጫው ስር ያለችውን ቡግር እያሻሸ ልማታዊ ጋዜጠኝነት ማለት ወደፊት ሊደረግ የሚችለው ነገር ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበራዊ፤ አዕምሮአዊ አካላዊ ፤ባህላዊ ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ለዚህም ነው ኢኮኖሚዊ ምክንያትን ብቻ መመልከት በጣም ውስን እንድንሆን ያደርገናል የሚባለው በዚህም የተነሳ ወደፊት ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮችን ወይም ሁኔታዎችን አስመልክቶ በመገናኛ ቡዙሃን ለማቅረብ የልማት ጋዜጠኞች ገደብ የለባቸውም፡፡
አሜሪካ እንደ አሁኑ ከመበልጸጓ በፈት ስትጠቀምበት የነበረው የሚዲያ ፍልስፍና ነው፡፡ ስለዚህ ከአደጉት ሀገሮች ደግሞ ማህበረሰባችን ብሎም ሀገሪቱን ከአለም ሚዲያ ተርታ ያሰለፋትን ፍልስፍና ብንከተል ምንድን ነው ጉዳቱ ብሎ ሲያፍተለተትል የነበረውን ቡግር አፍርጦ በመሀረብ ጠርግ ጠረግ ያደርጋል፡፡ ( እንደሱ ቡግር ችግሮችም አብረው ከነእውነታቸው ቢፈርጡ ጥሩ ነበር ታዲያ ምን ደርጋል አይሆንማ፡፡)
የጋዜጠኝነት ህይወት በማያቋርጥ በረራ ይመሰላል፡፡ እንደምታዩት ቢሮአችን ጸጥ ረጭ ብሎአል ጋዜጠኞቹ የማህበረሰቡን ችግር ነቅሰው አውጥተው ከችግሩ ገፈት ቀማሽ ሳይሆን በጊዜ ሊገላግሉት ሲሯሯጡ ነው የሚውሉት፡፡ ብሎ ደግፋቸው ቦርጩን ደገፍ ብሎ ቁጭ አለ፡፡ እኛም የስምዖንን አሜሪካ ልማታዊ ጋዜጠኝነት መቸ እና እንዴት እንደሰራች ባናውቅም የሱን የውሸት እውነት አጉርሶናል፡፡በነገራችን ላይ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይሆናል ይባላል አይደል ? ይህ አባባል ፈፅሞ ለኔ ሊዋጥልኝ አይችልም፡፡ እውነት ቢደጋገም ራሱ እንኳ እውነት እንጅ ሀቅ ሊሆንበት በማይቻልበት መንገድ እንዴት ውሸት ሲደጋገም እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ አይደለም ጋዜጠኛ መሆን የጋዜጠኝነት ተማሪ መሆን ራሱ ከቦታ ቦታ አዘዋውሮ በደርዘን የሚቆጠሩ ራዲዮ ጣቢያዎችን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በአጠቃላይ ህትመትና ብሮድካስት ሚዲያዎችን አስሰናል ዳሰናል፡፡ ከጉብኝቱ የተረዳሁት ነገር ቢኖር በርካታ ነገሮች ናቸው፡፡
ልክ እንደነ ስምዖን ደግፋቸው አንበርብርን አይነት በርካታ ገፀ-ባህሪያትና ልምድ ቀስሚያለሁ፡፡ በልብ-ወለድ ሆነም -ልብ ወለድ መፅሃፍት አብዛኛውን ጊዜ ማለት ይቻላል የማህበረሰቡ ችግር ነቃሾች ተብለውና ተቆጥረው ከሚነሱት መካከል የእብድ ባህታዊ ገፀ-ባህሪ የተላበሱ ሰዎች ናቸው፡፡ ልማታዊ ጋዜጠኝነትን ስናቀነቅን ከጋዜጠኛ እብድ ተሽሎ ማህበረሰቡን ወክሎ የሚጫወት ከሆነ ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ ነኝ እያለ በያመቱ የሚመረቀውና እንዲሁም በሞያው ላይ እየሰራ ያለ ባለሞያ አፈር በላው ብዬ ዝም አልሁ፡፡
ስምዖን በድጋሜ ፊቱን ጨፍገግ አድርጎ በግራ ፊቱ ያለውን ቡግር በግራ እጁ አያሻሸ ነገር ሳያውቁ ሙግት አቅም ሳይኖር ትዕቢት እናንተ እኮ የነገ የሀገሪቱ ተስፋናችሁ መንግስት ለሚዲያ እና ለጋዜጠኞች መብት ሰጥቷል፡፡ ሳንሱር የሚባል ነገር ፈፅሞ የለም፡፡ ብሎ ተቀመጠ፡፡ እንዳልካቸው ከወደ መቀመጫው ጦር የተወረወረበት ይመስል በፍጥነት ብድግ አለ፡፡ ስምዖን በድንጋጤ ሲያሻሻት የነበረውን ቡግር መሀረቡን ሳያዘጋጅ አፈረጠው፡፡እንዳልካቸው ቀጠለ እኛ የምንማረው እና አሁን ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ለዬቅል ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የሳንሱር ችግር ነው፡፡ ብሎ የተወረወረበት ጦር የተነቀለ ይመስል ተመልሶ ቁጭ አለ፡፡ በእድሜ ጠና ያሉት አንበርብር ከመቀመጫቸው ብድግ ብለው የተቀመጠውን ሰው በሙሉ በሙሉ ትኩር ብለው መመልከታቸውን ቀጠሉ፡፡ ስምዖን የተናገረው ሃሳብ አሳንሱር የለም ላለው ሃሳብ እኔ በድጋሜ ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው በመንግስት ደረጃ አሳንሱር የለም፡፡ ጋዜጠኛው ግን ፍርሃት አዕምሮውን የንግስ ካባ ስላለበሰው አሳንሱር አለ ብሎ ያምናል;;
አንተ አስተሳሰብህን ከቀዬርህ አለምን ትቀይራለህ፡፡ ሲባል ሰምታቹህ አታውቁም በቃ ዋናው ነጥብ ይሄ ነው!!! የመንግስት አካል ባለሀብት ባለህ ነገር ሊደራደሩህ ይችላሉ፤ የሞያው ፍቅር ካላቹህ አንተም ሚስትህም ልጅህም ለአንተ ምንም አይደሉ፡፡ ምክንያቱም አንተ ውስጥ ያለው መረጃ በቀላሉ የአንድ ሽህ ሰዎች ህይወት ልትታደግበት ትችላለለህና፡፡ የአንተ አንድ ነፍስ ከአንድ ሰው ህይወት ጋር ሲወዳደር ኢምንት ነው፡፡ እነደውም ከቁጥር አይገባም ገባህ!!!! ገባህ የሚለውን ቃል ሲናገሩ እንባ በአይናቸው ግጥም ብሎ ወደታች መፍሰስ ጀመረ፡፡
አንበርብር ከእንባው ጋር እየታገለ በዓሉ ግርማን የማያውቅ ጋዜጠኛም ሆነ የጋዜጠኝነት ተማሪ አይኖርም፡፡ ደራሲው በሚለው መፅሐፉ ላይ ደራሲው ሲራክን ባለቤቱ ቤት እንስራ እያለች ትጨቃጨቀው ነበር እርሱ ግን ነገ ትተነው ለምንሄደው ቤት አልጨነቅም ይል ነበር፡፡ በቃ የኔ ጀግና ደራሲውን የመሰሉ እንደ ሲራክ አይነት ገፀ-ባህሪያት የሚሆን ጋዜጠኛ ነው፡፡ደራሲውን ከአድማስ ባሻገር የህሊና ደወል ኦሮማይን የቀይ ኮከብ ጥሪና ሀዲስ የመሰሉ መፅሐፍ ጽፎ በሰው ልብ ውስጥ መንገስ ነው፡፡ የበዓሉ ግርማን መፅሐፍ አንብቦ በልቡ ውስጥ ቤት የማይሰራለት ማንም ሰው አይኖርም ምክንያቱም እኛ የምንኮላተፍባቸውን ቃላት ከመፈጠራቸው በፈት ይራቀቅባቸዋልና ነው፡፡ አኛ ግን በፍርሃት ካባ ተሸብበን ሞያችን አርክሰን ራሳችን ረክሰን ህብረተሰባችንን እናረክሳለን ፡፡ በስተመጨረሻም መንግስት፣ አሳንሱር እንላለን ብሎ ከኪሱ መሀረብ እያወጣ ተመልሶ ተቀመጠ፡፡
ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ አበው ጥልቅ እውቀትና ለሞያው ፍቅር ያለው ሰው ያምራል በስሜት ላይ ሁኖ ወደ ስሜት እንዲገቡ ኮርኩሮ አስገብቶ ጠጥ ረጭ ይላል፡፡ እኔም ጋዜጠኛውን ማንም አያሰፈራራውም ራሱ አዕምሮውን እሰከ ጥጉ መታገል አለበት፡፡ አለበለዚያ ብዕር ሲያነሳ፤
እዩት ያንን ጫሪ ያለቅጥ ሲደፍር
በመቃ - ብዕሩ መቃብሩን ሲቆፍር    ( ገጣሚ ሳሙኤል ተመስጌን )  ነው እንዴ ብሎ የሚቀመጥ ጋዜጠኛ ከሚፈጠር ቀድሞ ራሱን ቢሰዋ መርጣለሁ፡፡ በስተመጨረሻም እኔ በድፈርት ከመድረኩ ላይ ወጥቸ ጥሩ ጋዜጠኛ ቢፈጠርልኝ ብዬ በማሰብ
አንት ወሬ ቀማሚ የወጉም አለቃ
ቶሎ ድረስ እንጅ ነገር ሳያበቃ
በመቃ-ብዕርህ ታሪክን ከትበው
የዛሬው ጽሁፍህ ለነገ ድርሳን ነው፡፡
የሳሙኤልን የቡግር አስተሻሸት የደግፈቸውን በዜና መሸጥ ቦርጭ ተመልክቸ የአንበርብርን ወኔ ወደራሴ አሰተጋብቸ ከአዳራሹ ወጣሁ፡፡ **
*** መስከረም 2010 .


No comments:

Post a Comment