Friday, January 26, 2018

አንች ስትቀጥሪኝ

*** አንች ስትቀጥሪኝ ***

(በሙሉጌታ አንበርብር)



የነተበ ልብሴን ወደዚያ ወርውሬ
ሻንጣየ ገብቸ ባዲሱ ቀይሬ
እመጣልሽለሁ አንች ከጠብቅሽኝ
ዘግይቸ አላውቅም አንች ስትቀጥሪኝ
ግዴለም ግዴለም
ሻንጣየ ይሞላ በአደፋ ጨርቅ
አንችጋ ስመጣ ይመስለኛን ወርቅ
ኩታየን ለብሸ ወርቄን አገልድሜ እመጣልሽለሁ
ሰከንድ ደቂቃ ምታቸው ሳይጨምር እደርስልሻለሁ

አንች ስትቀጥሪኝ

ወንዙን ተሻግሬ ባህርን ቀዝፌ
ተራራን ሰንጥቄ ኮረብታን አልፌ
ካለሽበት ቦታ በሰከንዳድ እድሜ እደርስልሻለሁ
ምክንያቱም
ከራሴ አስበልጨ እኔ እወድሽለሁ

አንች ስትቀጥሪኝ

አበባ በለለበት በደረቀ ምድረ በዳ
መዓዛ ያውደኛል ያውም የፅጌረዳ
መዓዛ ያለው ነገር
ሽታ ያለው ነገር
አንች እንደምትወጅው እኔም እወዳለሁ
ምክንያቱም
አንች የወደድሽው እኔም እወዳለሁ

አንች ስትቀጥሪኝ


አንች የምትወጃት ጨረቃ ብጠፋ
ገበሬ የሚወደው ዝናቡ ቢያካፋ
ኤርፖርት የሚጠላው ጉሙ ቢንሰራፋ
ወንዝ ተሻጋሪ ሁሌም የሚጠላው ፈፋ ቢደነፋ
ከማሪያም መቀነት ይበልጥ ወድሻለሁ
ምክንያቱም
የማሪያም መቀነት መዳሰስ እሻለሁ
መዳሰሱን ብሻም ሁልጊዜ ብሳሳም
እንዳንች መዳሰስ አይቻለኝ መሳም::
አንች ስትቀጥሪኝ
*
*
*
*
አንች ስትቀጥሪኝ
*
*
*
*
አንች ስትቀጥሪኝ
*
*
*
*

@ላሊበላ 
11/11/2008 E.C

No comments:

Post a Comment